News

ፍርሳታ – ቅኝአገዛዝ ፊልም እና ስክሪን ጥናቶች

Amharic translation by Mike Thomas and Lideya Teshome, with input from Aboneh Ashagrie

የፊልም እና ስክሪን ጥናትና ትምህርት ከተጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት አንስቶ፣ በታሪካዊ፣ በንድፈ-ሃሳባዊ እና በሂሳዊ ማእቀፎች ውስጥ ብዙውን ጊዜ በምዕራባዊያን ተፅዕኖ ውስጥ ይታያል።

ምንም እንኳን “የዓለም ሲኒማ” እና የ“ትራንስናሽናል ሲኒማ” ምሁራን ቀኖናዎችን እና ማዕቀፎችን ለማስፋትጥረት ቢያደርጉም፣ በርካታ ዋና ዋና ችግሮች እንደቀድሞዉ ናቸዉ።

በተለይም በአፍሪካውያን የተሰሩ ፊልሞች እና ጥናቶች ሙሉ ለሙሉ ትኩረት ባይነፈጋቸዉም፣ የሚገለሉባቸዉጊዜያት ጥቂት አይደለም።

ይህ የፊልም እና ስክሪን ጥናት ፊልሞችን ለመስራት በቴክኖሎጅያዊ መንገድ ትልቅ መዳረሻ በሚሰጥበት እናበብዙ ስክሪን ላይ በማሰራጨት ረገድ ለ 21ኛው ክፍለ ዘመን የፊልም እና ስክሪን ጥናቶችን እንደገና ለመከለስየሚረዱ አስደሳች ለውጦች እንዳይኖሩ እንቅፋት ይፈጥራል። “ስክሪን ዓለማት” በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉናቸው።

ይህ ፕሮጀክት እነዚህን “ስክሪን ዓለማት” (በሁለቱም ጽሑፋዊ ቅርፃቸው እና በኢንዱስትሪ መዋቅሮቻቸው) ላይበማተኮር በአፍሪካ (በተለይም በናይጄሪያ እና በኢትዮጵያ) ላይ ከፍተኛ ትኩረት የተጎናፀፉትን የአህጉር ሲኒማየማሳየት መንገድ ነው።

እንዲሁም በዓለም፤ በዓለም በስተደቡብ የሚገኙ ሃገራት (በተለይም በአፍሪካ እና በእስያ መካከል) ተመሳሳይነት፣ልዩነቶች እና ትይዩ እድገቶችን በመመርመር የንፅፅር ጥናቶችን ዓለም አቀፋዊ “ስክሪን ዓለማት” እናብራራለን።

በትምህርታዊ መንገድ ብቻ ሳይሆን – በትላልቅ ስብሰባዎች እና ህትመቶች – እንዲሁም ሃሳቦችን በመፍጠር እናበማንሸራሸር መንገዶች በማሳየት – የፊልም እና የስክሪን ጥናቶች እንዲካተቱ ምላሽ እንሰጣለን። እንዲሁምበድምጽ አወጣጥ የምርምር ዘዴዎች (እንደ ኦዲዮ ቪዥዋል ትችት እና የፊልም ቀረፃ)። ወደ “ፍርሳታ – ቅኝአገዛዝ  (de-colonising)” ፊልም እና ስክሪን ጥናቶች (ሥርዓተ-ትምህርትን፣ ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፣እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወክል እና ግንዛቤ ማጓልበትን በማካተት ማስተማርን በተመለከተ ‘የመሣሪያ ኪትስ’ ምርት በማምረት)።

በሥነ-መለኮታዊ ደረጃ፣ የ“ስክሪን ዓለማት” (ወይም ሌሎች እሳቤዎች) ጽንሰ-ሀሳብ ውስብስብነት ለመዳሰስ ከ“ወርልድ ሲኒማ” ወይም “ትራንስናሽናል ሲኒማ” በተሻለ ሁኔታ የትኛው ብቁ መሆን አለመሆኑን፤ እንዲሁምዓለም አንድ እየሆነችበት ባለ የቴክኖሎጂ ዘመን ይሄ ስነ ሀሣብ እንዴት ከጊዜው ጋር አብሮ ይራመዳል የሚለውንሰፊ ጥናት እናደርግበታለን።

Share